እባክዎ በ +251 938 17 17 17 ወይም 6239 ይደውሉልን

ኤጋ 400 ቆርቆሮ

ስለ ኤጋ 400 ቆርቆሮ

የኤጋ 400 ቆርቆሮ ከኢትዮጵያን ስቲል ኃ.የተ.የግ.ማ (አንበሳ ቆርቆሮ) ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ የላቀ የጣሪያ መፍትሄ ሲሆን  የኢንደስትሪ፣ የንግድ እና የመኖሪያ ፕሮጀክቶችን ፍላጎት ለማሟላት የተነደፈ ነው። ስሪቱ በ 1 ሜትር ስፋት ቆርቆሮ ላይ ባለ 4-መንገድ የዝናብ ፍሰት ስርዓት የሚከተል ሲሆን, EGA400 የተሻለ የውሃ ፍሳሽ ወደ ገተር (አሸንዳ) ይልካል፣ ይህም ከባድ ዝናብ ላላቸው አካባቢዎች ተስማሚ ምርጫ ያደርገዋል፣ ዘመናዊው ንድፍ እና ጠንካራ መዋቅር የተሻሻለ ጥንካሬ እና የረጅም ጊዜ አፈፃፀምን ያቀርባል።

የኤጋ 400 ጣሪያ ባህሪ እና መገለጫ​

  • የተሻሻለ የዝናብ ፍሰት

    ባለ 4-መንገድ የዝናብ ፍሰት ስርዓት ፈጣን የውሃ ፍሳሽን ለቤቱ ይሰጣል፣ ፍሳሽን እና የውሃ መከማቸትን ይከላከላል።

  • ቆይታ

    ከቅድመ-ቀለም (በጥሬ እቃ ምርት ሂደት ውስጥ) የተቀባ ስቲል እና የአሉሚኒየም ዚንክ የተሰራ በመሆኑ EGA400 ልዩ ጥንካሬ እና ረጅም ጊዜ ይሰጣል።

  • እርጥበት እንዳያስተላልፍ የሚያደርግ ዲዛይን

    ኤጋ 400 ከ አንዱ ጋር በሚጎራረስበት ጊዜ ውሃ ያለማስገባት ጥንካሬን ይሰጣል፣ በከባድ ዝናብ ውስጥ እንኳን ምንም ፍሳሽ እንዳይኖር ያደርጋል።

  • ዝገትን እና አየር ንብረትን ይቋቋማል

    የተራቀቀው ሽፋን ከዝገት እና ከአልትራቫዮሌት መጋለጥ ይከላከላል ይህም ለተለያዩ የአየር ሁኔታ ተስማሚ ያደርገዋል።

  • ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የቆርቆሮ ገጠማ

    EGA 400 ቦዮቹ ልክ እንደ ኤጋ 300 ሰፋ ሰፋ ያሉ ስለሆኑ ለፈጣን ገጠማ የተስማማ ነው፣ የሰራተኛ ወጪን በመቀነስ እና ንጹህ እና እንከን የለሽ እይታም ይፈጥራል።

  • ውበት

    የተለያዩ የሕንፃ ንድፎችን እውን ለማድረግ በበርካታ ቀለሞች እኛ ጋር ይገኛል።

የ EGA 400 ጥቅሞች እና አገልግሎቶች

ለመጋዘኖች – ለኢንዱስትሪ ተቋማት ለመጋዘን እገልግሎት መዋል የሚችል ሲሆን የአየር ሁኔታን ይቋቋማል።

ዩኒቨርሲቲ ማደሪያ -ለተማሪዎች መኖሪያ ቤት አስተማማኝ መጠለያ ይሰጣል።

የመኪና ማቆሚያ ህንጻዎች – መኪናዎችን ከፀሀይ እና ከዝናብ ይከላከላል።

ቨራንዳ – ቆንጆ እና ዘላቂ የቤት ውጭ ቦታዎችን ይፈጥራል።

EGA400 – የመጨረሻው የጣሪያ መፍትሄ

ለትልቅ የኢንዱስትሪ መጋዘኖች ወይም ዘመናዊ የመኖሪያ ፕሮጀክቶች EGA400 ከፍተኛ ጥንካሬን፣ ቅልጥፍናን እና ዘላቂነትን ያረጋግጣል። የአየር ሁኔታን የሚቋቋም ስለሆነ እንዲሁም በዘመናዊነቱ EGA400 ተመራጭ ነው።

ምናባዊ የቆርቆሮ ንድፍ

መስራት ያሰቡትን ቤትዎን ከታች በመጫን ቀድመው ይዩት

ቴክኒካል መግለጫ​

የኛን ሙያዊ እርዳታ ይፈልጋሉ?