እባክዎ በ +251 938 17 17 17 ወይም 6239 ይደውሉልን
ደንበኞች ለተፈለገውን የምርት አይነት እና ቀለም ይመርጣሉ።
የሚፈልጉትን ቆርቆሮ እንደመረጡ በ 1 ቀን ውስጥ የራሳችንን ለኪ ልከን ትክክለኛውን ልኬት በመውሰድ ምን ያህል ቆርቆሮ እንደሚያስፈልግ እናረጋግጣለን፣ ነገር ግን እርስዎ በባለሙያ ቀድመው ካስለኩ በሱ መሰረት የሚያስፈልገውን የቆርቆሮ ብዛት ከአጠቃላይ ክፍያ ጋር እንነግርዎታለን
የሚያስፈልጉትን መረጃዎች ማለትም ቲን ቁጥር (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)፣ እና ቢያንስ 50% የከፈሉበትን ደረሰኝ ሲያመጡ ወዲያው ወደ ሲስተሙ ውስጥ በመክተት ምርቱ እንዲጀመር እናደርጋለን
ሁሉም መረጃ ከተሟላ በዋላ ምርቱ ከመጀመሩ በፊት ሙሉ ክፍያ እንደከፈሉ ምርቱ ምጀመራል፣ ወዲያውም ተመርቶ የሚያልቅ ይሆናል።
የምርት ሂደቱ 1 ቀን ብቻ የሚፈጅ ሲሆን ምናልባት ግን የእርስዎ ትዛዝ በጣም ብዙ ከሆነ ምናልባት 2 ቀን ይቆያል፣ ልክ እንዳለቀ ደውለን የምናሳውቅዎ ይሆናል፣ ከዛም በመቀጠል ምርትዎን አዲስ አበባ ካሉ እና ሌሎች ቢያንስ 3 ትዛዝ ካሉ በራሳችን መኪና በነጻ የምናደርስ ይሆናል በጣም ከቸኮሉ ግን በርስዎ መኪና ምርቱን መረከብ ይችላሉ