እባክዎ በ +251 938 17 17 17 ወይም 6239 ይደውሉልን

ኤጋ 600 ቆርቆሮ

ስለ ኤጋ 600 ቆርቆሮ

አንበሳ ቆርቆሮ የEGA600 የጣሪያ ሽፋን ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ ከሌሎቹ ቆርቆሮዎች በጎን ሰፊ የሆነ የጣሪያ መፍትሄ ሲሆን ለከፍተኛ ሽፋን እና ለቅልጥፍና የተሰራ ነው። ባለ 6 መንገድ የዝናብ ፍሰት ስርዓት ያለው ሲሆን፣ ኤጋ600 ወደር የለሽ የውሃ ፍሳሽ ያቀርባል፣ ይህም የመንጠባጠብ እና የውሃ የመጠራቀም ችግርን ያስወግዳል። የ 1220 ሚሜ ስፋት ያለው ሲሆን ለትላልቅ የኢንዱስትሪ፣ የንግድ እና የመኖሪያ ፕሮጀክቶች 1 ቆርቆሮ የሚይዘው ቦታ ሰፋ ስለሚል የሚፈለጉትን የቆርቆሮ ብዛት በመቀነስ ወጪ ቆጣቢ ምርጫ ያደርገዋል። የላቀ ጥንካሬ፣ ዘመናዊ ውበት ያለው ሲሆን የሸካራ እና በለስላሳ አማራጮች ከቀለማት አማራጭ ጋር ያገኙታል።

የኤጋ600 ጣሪያ ባህሪ እና መገለጫ​

  • የተሻለ የዝናብ ውሃ ፍሳሽ

    ኤጋ600 ባለ 6-መንገድ የዝናብ ፍሰት ስርዓት ሳላለው የውሃ መከማቸትን በመከላከል የተሻሻለ የውሃ አያያዝ ያለው ሲሆን ጥሩ የውሃ ፍሰትን ይሰጣል።

  • በ 1 ቆርቆሮ ሰፊ ቦታ መያዝ የሚችል

    በ1220 ሚሜ ስፋት ስላለው EGA600 ተጨማሪ ቦታን ይሸፍናል፣ የመጫኛ ጊዜን እና በጭነት ወቅት መደራረብን ይቀንሳል።

  • ጥንካሬ እና ቆይታ

    ኤጋ600 ከ ቅድመ-ቀለም (በጥሬ እቃ ምርት ሂደት ውስጥ) የተቀባ ሲሆን እንዲሁን በውስጡ ጋልቫናይዝድ፣ ዚንክ እና አልሙኒየም ስላላቸው ከፍተኛ የሆነ ከዝገት የመከላከል አገልግሎት ይሰጣሉ እንዲሁም ከባድ ለሚባል የእየት ሁኔታ ተመራጭ ናቸው።

  • የሸካራነት አማራጮች

    በሁለቱም ለስላሳ እና በሸካራ/በሮያል አጨራረስ (ፊኒሺንግ) የሚገኝ ሲሆን ኤጋ600 ለዘመናዊ ቤቶች ተመራጭ ናቸው።

  • በመግጠም ጊዜ ፈጣን እና ወጪ ቆጣቢ

    ጎኑ ሰፊ ነው ማለት አነስተኛ ቆርቆሮዎች ናቸው ለቤቱ የሚያስፈልገው ማለት ነው። ይህም ማለት የሰው ኃይል ወጪ ይቀንሳል በተጨማሪም ጭነቱን ፈጣን እና ቀልጣፋ ያደርገዋል።

  • ለማራኪ ውበት

    በተለያዩ ቀለማት እና በሸካራነት አማራጭ የሚገኘው EGA600፣ የተለያዩ የስነ-ህንፃ የቆርቆሮ ፍላጎቶችን ያሟላል፣ እንዲሁም ለማንኛውም ፕሮጀክት ቆንጆ እና ዘመናዊ መልክን ይሰጣል።

የ EGA 600 ጥቅሞች እና አገልግሎቶች

✅ ለመጋዘኖች – ለኢንዱስትሪ ተቋማት ለመጋዘን አገልግሎት መዋል የሚችል ሲሆን በተሻለ መንገድ የአየር ሁኔታን ይቋቋማል።

ለዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክቶች -ለተማሪዎች መኖሪያ ቤት አስተማማኝ መጠለያ ይሰጣል።

✅ የመኪና ማቆሚያ ህንጻዎች – በ ሕንጻዎች የሚገኙ መኪናዎችን ከፀሀይ እና ከዝናብ ይከላከላል።

✅ ለቨራንዳ – ቆንጆ እና ዘላቂ የቤት ውጭ ቦታዎችን ይፈጥራል።

ለዘመናዊ የመኖሪያ ፕሮጀክቶች ወይም ትልቅ የኢንዱስትሪ መጋዘኖች EGA600 ከፍተኛ ጥንካሬን፣ ቅልጥፍናን እና ዘላቂነትን ያረጋግጣል እንዲሁም በስፋት አማራጭ እና በሸካራነት አማራጭ መገኘቱ ከሌሎቹ በተሻለ ተመራጭ ያደርገዋል። የአየር ሁኔታን የሚቋቋም ስለሆነ እንዲሁም EGA600 ተመራጭ ነው።

ምናባዊ የቆርቆሮ ንድፍ​

መስራት ያሰቡትን ቤትዎን ከታች በመጫን ቀድመው ይዩት

ቴክኒካል መግለጫ

የኛን ሙያዊ እርዳታ ይፈልጋሉ?​